Fana: At a Speed of Life!

አትሌት ታምራት ቶላ  ከአምስተርዳም  ማራቶን ውድድር ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ34 ዓመቱ አትሌት ታምራት ቶላ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ከ50ኛው የአምስተርዳም ማራቶን ውድድር ውጪ ሆኗል።

ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳረጋገጠው፤ የአምስተርዳም ማራቶን ክብረ ወሰን ባለቤት አትሌት ታምራት ቶላ ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት ነው ከውድድሩ ውጪ የሆነው።

የኦሊምፒክ እና የዓለም ሻምፒዮን ባለድሉ አትሌት ታምራት ቶላ በገጠመው ጉዳት ምክንያት በቅርቡ በጃፓን ቶኪዮ በተካሄደው 20ኛው የዓለም ሻምፒዮና ላይ ሳይሳተፍ መቅረቱ ይታወሳል።

ከታምራት ቶላ በተጨማሪ አትሌት ሙክታር  ኢድሪስ  በግል ጉዳይ ምክንያት በውድድሩ እንደማይካፈል ተገልጿል።

የአምስተርዳም ማራቶን የቦታው ክብረ ወሰን በወንዶቹ በአትሌት ታምራት ቶላ 2:03:38፤ በሴቶቹ  ያለምዘርፍ የኋላው 2:16:52 መያዙ ይታወቃል።

በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ ያለው የአምስተርዳም ማራቶን የፊታችን እሁድ ሲካሄድ 60 ሺህ ተሳታፊዎች ይካፈሉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በወርቅነህ ጋሻሁን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.