በሐረሪ ክልል የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሐረሪ ክልል የሕዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው አሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ፡፡
አቶ ኦርዲን እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በሐረሪ ክልል እውን የተደረጉና እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ በ2018 የበጀት ዓመት በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የሕዝብን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
የልማት ሥራዎቹ የሐረሪ ክልልን የማንሠራራት ጅማሮ የሚያመላክቱ እና የሕዝብን ኑሮ የሚቀይሩ ናቸው ብለዋል፡፡
ሕዝብን በማሳተፍ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን በፍጥነት እና በጥራት ለማጠናቀቅ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡
በሒደት ላይ የሚገኙ ነባር ፕሮጀክቶች በሚፈለገው የጥራት ደረጃና የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠናቀቁ የሚያስችል አቅጣጫ መቀመጡን ጠቅሰዋል።
ተጠናቅቀው አገልግሎት መስጠት ያልጀመሩ ፕሮጀክቶች ደግሞ በአፋጣኝ ወደ ሥራ ገብተው አገልግሎት መስጠት እንዲጀምሩ አሳስበዋል፡፡
ከአጠቃላይ የክልሉ በጀት 53 በመቶ የሚሆነው ለኢኮኖሚ ዘርፍ መመደቡን ጠቁመው÷ ይህም የሕዝብን ኑሮ ከማሻሻል ባለፈ ለቀጣዩ ትውልድ ምንዳን ማውረስ ያስችላል ነው ያሉት፡፡
በተስፋዬ ሃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!