Fana: At a Speed of Life!

ሀገር የሚሰራው በትውልድ ቅብብሎሽ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሀገር የሚሰራው በአንድ ትውልድ ብቻ ሳይሆን በትውልድ ቅብብሎሽ ውስጥ ነው አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሶፍ ዑመር ወግ በሚል ርዕስ ከቀድሞ እና በሥራ ላይ ካሉ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት÷ ሀገር በአንድ ትውልድ ብቻ ሳይሆን በትውልድ ቅብብሎሽ እንደሚሰራ አመላክተዋል።

ትውልዶች በሦስት እንደሚከፈሉ ገልጸው÷ የመጀመሪያው ያለፈው በመባል የሚታወቅ ትውልድ እንደሆነና ትላንት የተከሏቸው ዛፎች፣ ያስቀመጧቸው ብሎኬቶች፣ የጣሏቸው ዐሻራዎች እና እሳቤዎች ያሏቸው መሆናቸውን አንስተዋል።

ሁለተኛው አሁን ያለው ትውልድ በመባል የሚታወቀው እንደሆነና ግማሽ ማንነቱ ከመጀመሪያው ትውልድ እሳቤዎች የተወሰደ እንደሚሆን አስረድተዋል።

ሦስተኛው ደግሞ የሚመጣው ትውልድ በመባል እንደሚታወቅ ገልጸው÷ ከእኛ የሰማውንና የተመለከተውን በመውሰድ ማንነቱን እንደሚቀርጽ እንዲሁም የትውልዶችን ደም ብቻ ሳይሆን እሳቤንም የሚጋሩ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ይህንን ጉዳይ መካድ ችግር እየፈጠረ እንደሚገኝ አንስተው÷ ትናንት በእኛ ላይ ጥላ እንዳለው እያመንን ስንሄድ ሀገር ለመስራት ያለን ብቃት እየሰፋ ይሄዳል ብለዋል፤

ተፈጥሯዊ የሆነው ነገር የማይቀር መሆኑን አምኖ መቀበል እንደሚያስፈልግ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ አሁን የምትገኙ ሰዎች ዕድለኛ መሆናችሁን በመረዳት በዚሁ ሂደት ከመሄድ ውጪ ለብቻ ሀገር እሰራለሁ ብሎ ማሰብ እንደማይቻል አስረድተዋል።

ባሰቡት መንገድ መጓዝ ካልተቻለ ልማት እና ብልጽግናን ማምጣት እንደማይቻል እና እሳቤውን መጓዝ እንደሚገባም አጽንዖት ሰጥተዋል።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.