ለግብርና ዘርፍ እመርታዊ ውጤት የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ሚና
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በግብርና ዘርፍ እመርታዊ ውጤት ለማምጣት በሚደረገው ጥረት የድርሻዬን ለመወጣት እየሰራሁ ነው አለ።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ር) ለፋና ዲጂታል እንዳሉት÷ ተቋሙ ከምስረታው ጀምሮ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጂዎች በማፍለቅ አርሶ አደሮችን ጨምሮ ለግብርና ተዋናዮች እያደረሰ ይገኛል።
በዚህም እስካሁን 1 ሺህ 600 ያህል የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በማውጣት ጥቅም ላይ እንዲውሉ አድርጓል ብለዋል።
ኢንስቲትዩቱ በጥናትና ምርምር፣ ቴክኖሎጂዎችን በማሰራጨት፣ አገልግሎትና ድጋፍ በመስጠት፣ አሰራር እና ማሻሻያዎችን ተደራሽ በማድረግ እንዲሁም የተሳለጠ የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር በመስራት ለግብርና ዘርፍ እመርታዊ ለውጥ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በጥናትና ምርምር ለሁሉም ወቅቶች እና ሥነ ምህዳሮች ተስማሚ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን እያጠና እና እያዳበረ እንደሆነ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ÷ በምርምር የተገኙ ቴክኖሎጂዎችን በማድረስ ተገቢው ውጤት እንዲመጣ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
ቴክኖሎጂዎች ከሥነ ምህዳር ጋር ያላቸው ተስማሚነት እና ማህበራዊ ተቀባይነት ከግምት ውስጥ ገብቶ እንደሚፈልቁ ገልጸዋል።
በተለይም የምግብና የንጥረ ምግብ ዋስትና፣ የውጭ ገበያ ፍላጎት፣ የኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ግብዓትነት እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን መተካት ላይ ትኩረት በማድረግ ምርምር ይካሄዳል ነው ያሉት።
በሰብል ልማት ላይ በሚደረጉ የምርምር ስራዎች የውሃ ፍላጎትን ጨምሮ የተሻሻሉ ዝርያዎች የሰብል ክብካቤና ጥበቃ፣ የአፈር ለምነትና ጤንነት የተሟሉ መሆናቸው እንደሚረጋገጥ አመልክተዋል።
የምርምር ስርዓቱ የሚያወጣቸውን ቴክኖሎጂዎች ወደ ምሉዕ የምርት ፓኬጅ በመቀየር ሰርቶ በማሳየት እና በቅድመ ማስፋት መርሐ ግብር ያሰርጻል ብለዋል።
እንደ ንጉሴ ደቻሳ (ፕ/ር) ገለጻ÷ ኢንስቲትዩቱ ግብርና ሚኒስቴርን ጨምሮ ከሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ጋር ተቀናጅቶ በመስራት ለዘርፉ እመርታዊ ውጤት የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል።
በአቢይ ጌታሁን
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!