አሜሪካ እና ህንድ በመከላከያ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ እና ህንድ በመከላከያ ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
በሀገራቱ መካከል የተደረገው ስምምነት በመጪዎቹ 10 ዓመታት ውስጥ የመከላከያ ትብብርን ለማስፋት የሚያስችል ነው፡፡
ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተደረጉት ተከታታይ ስምምነቶች ውስጥ የቅርብ ጊዜ ሲሆን ህንድ እና አሜሪካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመከላከያ ግንኙነታቸውን እያሳደጉ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡
የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት ስምምነቱ መቀናጀትን፣ የመረጃ ልውውጥን እና የቴክኖሎጂ ትብብርን የሚያጎለብት ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡
የህንድ የመከላከያ ሚኒስትር ራጅናት ሲንግ በበኩላቸው ስምምነቱ እያደገ የመጣው የሀገራቱ ስልታዊ መቀራረብ ምልክት መሆኑን ጠቅሰው፤ በመጪዎቹ 10 ዓመታት የመከላከያ ዘርፍ ስምምነት የሁለትዮሽ ግንኙታቸው ዋና ምሰሶ እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡
ስምምነቱ በቅርብ ወራት ውስጥ ህንድ ከአሜሪካ የምትገዛውን የኃይል እና የመከላከያ ግዢዎች እንደምትጨምር ፍንጭ የሰጠ ስምምነት ነው ተብሏል፡፡
ይህ ስምምነት ባለፈው ነሐሴ ወር መጠናቀቅ የነበረበት ቢሆንም ህንድ ከፓኪስታን ጋር ያለውን ግጭት በማስቆም ረገድ ስላለው ሚና የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሰጡት መግለጫ ላይ ባሳየችው አቋም መዘግየቱ ነው የተገለፀው፡፡
በሀገራቱ ስምምነት ያላቸውን የመከላከያ ግንኙነት በተመለከተ አጠቃላይ የፖሊሲ አቅጣጫ ይሰጣል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!