Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባንያዎች በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና ስራ እንዲጀምሩ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባንያዎች በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና ስራ እንዲጀምሩ ጥሪ ቀርቧል፡፡

የኢንዱትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር) በፈረንሳይ ፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ ከተገኙ የአውሮፓ እና የፈረንሳይ ኩባንያ ባለቤቶች ጋር ተወያይተዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው በዚሁ ወቅት ባለሀብቶቹ በድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጣና ሀብታቸውን እና ዕውቀታቸውን ስራ ላይ ለማዋል ከወሰኑ ኮርፖሬሽኑ ደረጃውን የተጠበቀ መሰረተ ልማት እና የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደሚያቀርብ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በትራንስፖርት፣ በሎጂስቲክስ እና መሰረተ ልማት ዘርፍ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮችም አብራርተዋል፡፡

በኢትዮጵያ እያደጉ የመጡ ሀገራዊ ስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንቶችን እድገት ለመደገፍ የሚያስፈልጉ የትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ ዘርፍ ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጋቸውን አስረድተዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው 14 ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች እና ፓርኮች ውስጥ ከ200 በላይ የሚሆኑ ኩባንያዎች በስራ ላይ እንደሚገኙ ነው የተገለጸው፡፡

በተጨማሪም ኩባንያዎቹ ከ100 ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ እድል መፍጠራቸው በኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ በለጠ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.