ፌዴሬሽኑ የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን አባልነት ማረጋገጫ ተሰጠው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን አባል የሆነበትን የአፍሪካ ባህል ስፖርቶች ኮንፌዴሬሽን የአባልነት ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት በዛሬው ዕለት ተሰጠው።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ወ/ሮ ህይወት መሃመድ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ÷ ጥያቄው አስቀድሞ ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅሰው÷ በዚምባብዌ ሃራሬ ከተማ በተካሄደው ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬት መረከባቸውን ተናግረዋል።
አባልነቱ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር ድንበር ተሻጋሪ የሆነ ግንኙነቶችን በመፍጠር ባህላዊ ስፖርቶቻችንን ለማስተዋወቅ ይረዳል ብለዋል።
በ1977 ዓ.ም የተመሰረተው የኢትዮጵያ ባህል ስፖርቶች ፌዴሬሽን የኢትዮጵያዊያን ባህላዊ ስፖርቶችና ጨዋታዎች በጥናትና ምርመር በመለየት ይዘታቸውን ጠብቀው ለትውልድ እንዲተላለፉ የማስተዋወቅ ስራዎችን እየሠራ ይገኛል።
በሙባረክ ፋንታው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!