ሀዋሳ ከተማና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሀዋሳ ከተማን ግብ ያሬድ ብሩክ አስቆጥሯል፡፡
አዲስ ግደይ ደግሞ የንግድ ባንክን የአቻነት ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ሸገር ከተማና ሀድያ ሆሳዕና ያደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቅቋል፡፡