Fana: At a Speed of Life!

ጥላሁን አመዴ (ፕ/ር) በግብርናው ዘርፍ ዓለም አቀፍ ሽልማት ተበረከተላቸው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ጥላሁን አመዴ (ፕ/ር) በግብርናው ዘርፍ የ2025 የአፍሪካ ግብርና ባለራዕይ ሳይንቲስት በሚል ዓለም አቀፍ ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡
ጥላሁን (ፕ/ር) ሽልማቱ የተበረከተላቸው በአፈር ጤና፣ የአየር ጸባይን ታሳቢ ያደረገ ግብርናን ለማከናወን እና ቀጣይነት ያለው የምግብ ሥርዓትን በአፍሪካ እውን ለማድረግ በሰሩት ስራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለጥላሁን አመዴ (ፕ/ር) የተበረከተላቸው ዓለም አቀፍ ሽልማት የመጀመሪያው ጥቁር አፍሪካዊ እንደሚያደርጋቸውና ለኢትዮጵያም ትልቅ ስኬት እንደሆነ ተመላክቷል፡፡
በተለይም በግብርናው ዘርፍ እየተሰጠ ያለው አመራር እያደገ መምጣቱንና በዘርፉ ፈጠራንና ኢኮ ቱሪዝምን ለማሳደግ እየተሰራ ያለውን ስራ የሚያበረታታ መሆኑም ተጠቁሟል።
ሽልማቱ የተበረከተላቸውም ከአሜሪካ የአፈር ሳይንስ ሶሳይቲ ነው።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.