Fana: At a Speed of Life!

በሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ እየተጫወቱ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ከ17 ዓመት በታች የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ ጨዋታቸውን እያደረጉ ነው።

ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በሚረዳው የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በዛሬው ዕለት መካሄድ ጀምሯል።

በውድድሩ 10 የሴካፋ ዞን አባል ሀገራት የሚፎካከሩ ሲሆን÷ የምድብ ጨዋታዎች አዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም እና ድሬዳዋ ስታዲየም ነው የሚካሄዱት።

ዛሬ በተጀመረው ውድድር ሩዋንዳ ከኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጨዋታ ከ10 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።

እንዲሁም ቀን 7፡00 ላይ በተካሄደው የመክፈቻ ጨዋታ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን 2 ለ 2 በሆነ የአቻ ውጤት ተለያይተዋል።

የዛሬው መርሐ ግብር ቀጥሎ ሲካሄድ 11:00 ታንዛኒያ ከ ሱዳን እንዲሁም ምሽት 2:00 ቡሩንዲ ከ ዩጋንዳ በድሬዳዋ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.