የወጪ ንግድ እንዲሳለጥ የሚያደርግ ከባቢን መፍጠር…
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የወጪ ንግድ እንዲሳለጥ የሚያደርግ ከባቢን ለመፍጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትብብር መስራት ይገባቸዋል።
የምጣኔ ሃብት ባለሙያ ዮሐንስ በቀለ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት÷ ኢትዮጵያን ከዕዳ ጫና በዘላቂነት ለማላቀቅ የውጭ ምንዛሪ ክምችትን ማሳደግ ወሳኝ ነው።
ለዚህም የወጪ ንግድን ማሳደግና የውጭ ምንዛሪ ክምችትን መጨመር እንደሚያስፈልግ አንስተው÷ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን መጨመርና የገበያ መዳረሻዎችን ማስፋት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ከማብዛት ባሻገር ዕሴት ጨምሮ በመላክ ላይ ትኩረት ማድረግ ያፈልጋልም ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በሀገር ውስጥ የማምረቻ ወጪን መቀነስ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው÷ ለዚህም የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የትራንስፖርትና ሌሎች ዘርፎችን በማስፋት ረገድ መንግስት ከፍተኛ ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
እየተሰሩ የሚገኙ መዋቅራዊ ሪፎርሞች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ በመግለጽ የንግድ እንቅስቃሴ እንዲሳለጥ የሚያደርግ ከባቢን በማስፋትና በማጠናከር የወጪ ንግድ እንቅስቃሴን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።
በዮናስ ጌትነት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!