የኢትዮጵያ እግር ኳስ ልማት በቅርቡ ብርቱ ተፎካካሪ ለመሆን ያስችላል – ቤንጃሚን ዚመር
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የጀመረችው የእግር ኳስ ልማት በቅርቡ በታላላቅ መድረኮች ተፎካካሪ የሚያደርጋት ነው አሉ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በ2ኛው የምድብ ጨዋታ ደቡብ ሱዳንን 4 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፉ ይታወቃል፡፡
ይህን ተከትሎ ከፋና+ ጋር ቆይታ ያደረጉት አሠልጣኝ ቤንጃሚን ÷ ጨዋታውን ባቀድነው ልክ ተቆጣጥረን ተጫውተናል ብለዋል፡፡
ይህም ተጋጣሚያችን ደቡብ ሱዳን ላይ ብልጫ ወስደን እንድናሸንፍ ረድቶናል ነው ያሉት፡፡
በኢትዮጵያ ትልቅ የእግር ኳስ አቅም እንዳለ ተመልክቻለሁ ያሉት አሠልጣኙ ÷ መንግስት እንዲሁም የሀገሪቱ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ለስፖርቱ ልማት የሰጡት ትኩረት አበረታች መሆኑን ጠቅሰዋል።
በአሁን ሰዓት አዳጊዎች ላይ እየተሠራ ያለው ሥራ ኢትዮጵያን በቅርቡ በአህጉር ከፍ ሲልም በዓለም አቀፍ መድረኮች ተፎካካሪ ሊያደርጋት እንደሚችል አመልክተዋል፡፡
የኢትዮጵያን ባለተሰጥኦ አዳጊዎች አቅም በአግባቡ ለመጠቀም በፕሮጀክት ታቅፈው ተገቢ ስልጠና መስጠት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን ከምድቡ ያደረጋቸውን ሁለት ጨዋታዎች በማሸነፍ በ6 ነጥብ ምድቡን እየመራ ይገኛል፡፡
በሙባረክ ፋንታው
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!