ኢትዮጵያ ያላት የተፈጥሮ ገፀ በረከት ለቱሪዝም ኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርጋታል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮ-ሳዑዲ ቢዝነስ ፎረም ተሳታፊ የሳዑዲ አረቢያ ልዑካን ቡድን አባላት ኢትዮጵያ ያላት የተፈጥሮ ገፀ በረከት ለቱሪዝም ኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርጋታል አሉ።
የልዑካን ቡድን አባላቱ የቤኑና መንደርን ጨምሮ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው ኢትዮጵያ ለቱሪዝም ኢንቨስትመንት ምቹ መሆኗን መመልከታቸውን ገልጸው፤ የቱሪስት መዳረሻዎቹ ጉብኝት የውጭ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑን ተናግረዋል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የቱሪዝም ዘርፍ እንደ ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶ ተወስዶ ዘርፉን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።
በዛሬው እለት ቤኑናን ጨምሮ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች በሳዑዲ ልዑካን አባላት መጎብኘቱ በኢትዮጵያ በቱሪዝም ኢንቨስትመንት እንዲሰማሩ አማራጮችን የሚያመላክት እንደሆነም ተናግረዋል።
የሳዑዲ አረቢያ ልዑካን ቡድን አባላት በበኩላቸው በጉብኝታቸው ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ገፀ በረከት የተቸረች ሀገር መሆኗብ መመልከቷን ገልጸው፤ ይህም ለቱሪዝም ኢንቨስትመንት ተመራጭ ያደርጋታል ብለዋል።
በቱሪዝም ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ለሚያፈስሱ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
በሔብሮን ዋልታው