ኢትዮጵያ በምርት ተወዳዳሪ እንድትሆን ትኩረት የተሰጠው ጥራት …
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በምታመርታቸው ምርቶች ተወዳዳሪ እንድትሆን የጥራት ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸዋል አሉ።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ለ14ኛ ጊዜ የዓለም የጥራት ሳምንትን የጥራት ማረጋገጫ የተሰጣቸውን ከ150 በላይ ድርጅቶች በማሳተፍ በጥራት መንደር ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሕዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ያከብራል።
ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በመርሐ ግብሩ መክፈቻ ላይ እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ የምርት ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነች ነው።
ከሚከናወኑት ተግባራት መካከል የጥራት ስራዎች ትኩረት እንደተሰጣቸው ገልጸው፤ ማምረት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የምርቶች ጥራት ትልቁ መመዘኛ ስለመሆኑ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከዓለም የንግድ ድርጅት ጀምሮ በብዙ ተቋማት ተወዳዳሪ ለመሆን የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውንም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር መዓዛ አበራ (ኢ/ር) በበኩላቸው፤ አንድ ምርት ለታለመለት ዓላማ ማዋል አንዱ የጥራት መለኪያ ነው ያሉት።
በቅድስት ተስፋዬ