Fana: At a Speed of Life!

ኢንስቲትዩቱ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያከናወናቸውን 56 ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶች በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ተደራሽ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያከናወናቸውን 56 ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶች በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ተደራሽ አድርጓል አሉ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)።

በዘርፉ የወጣቶች ግንዛቤና ተሳትፎ እንዲጠናከር የተለያዩ መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት በ2013 ዓ.ም ከተመሰረተ ጀምሮ ባለፉት አምስት ዓመታት አመርቂ እድገት አስመዝግቧል፡፡

ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ኢንስቲትዩቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በማደራጀት ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር መቻሉን ገልጸው÷ በዚህም ተወዳዳሪና ችግር ፈቺ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ለአብነትም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ 56 የምርምር ውጤቶችን በዓለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ ማሳተሙን አንስተዋል።

ከምርምር ውጤቶቹ መካከል ዘጠኙ የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ እንዳገኙ ጠቅሰው÷ ይህም ስኬት በሌሎች የምርምር ውጤቶች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

በርካታ ሀገራት በጤና፣ በግብርና እና በአገልግሎት ዘርፎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን በመጠቀም ምርታማነትን በእጥፍ በማሳደግ እና አገልግሎት አሰጣጣቸውን በማዘመን ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

በመሆኑም በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ የሀገሪቱና የሕብረተሰቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ በትውልድ ላይ መስራት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

በዘርፉ ያለው የወጣቶች ግንዛቤና ተሳትፎ እንዲጠናከር የተለያዩ መርሐ ግብሮችን በማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት 200 ጀማሪ የፈጠራ ባለሙያዎች በኢንስቲትዩቱ የስታርት አፕ ፕሮግራም ተካተው እየሰሩ ይገኛሉም ነው ያሉት።

ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር በዘርፉ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ የሰለጠነ በቂ የሰው ኃይል ለማፍራት የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዋና ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

‘ኢንተሊጀንስ ለሁሉም’ በሚል መሪ ሀሳብ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በሁሉም ሴክተሮች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.