የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አኖሩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ ዎንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በቀጣይም ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ የመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት ለጥቁር ሕዝቦች ነጻነት ትግል ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች መታሰቢያ ሐውልት ሥር የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጠቅላይ ሚኒስትር ሎውረንስ በምድረ ቀደሞቷ ኢትዮጵያ እንዲሁም በውቧ ከተማ አዲስ አበባ የሚኖራቸው ቆይታ ፍሬያማ እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!