ከ17 ዓመት በታች የሴካፋ ዋንጫ ኢትዮጵያ ከኬንያ የሚያደርጉት ጨዋታ በፋና+
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ዋንጫ (ሴካፋ) ማጣሪያ ውድድር ከምድባቸው ማለፋቸውን ያረጋገጡት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ዛሬ 10፡00 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ።
ጠዋታው በፋና+ ቴሌቪዥን ቻናል እና በፋና ዲጂታል አማራጮች በቀጥታ ይተላለፋል።
እኩል 7 ነጥብ በመሰበስብ ለግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠው ወደ ሜዳ የሚገቡት ሁለቱ ቡድኖች ምድቡን በበላይነት ለማጠናቀቅ ይፋለማሉ።
በግብ ክፍያ በመብለጥ ምድቡን የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአበበ ቢቂላ ስታዲየም የመጨረሻውን የምድብ ጨዋታ ቀን 10፡00 ላይ ያከናውናል።
ሰኞ ሕዳር 15 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው የኬንያ እና የደቡብ ሱዳን ጨዋታ በኬንያ 2 ለ 0 አሸናፊነት መጠናቀቁ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አንድ ጨዋታ እየቀረው ለግማሽ ፍጻሜ ማለፉን ማረጋገጡ ይታወሳል።
ከዚህ ጋር በተገናኘ ዛሬ በሚካሄዱ የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ቀን 7፡00 ሰዓት ላይ ደቡብ ሱዳን ከሩዋንዳ ሲገናኙ ቀን 10፡00 ሰዓት ላይ ሱዳን ከብሩንዲ እንዲሁም ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ኡጋንዳ ከጅቡቲ ይጫወታሉ።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!