ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 32ኛው የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ32) ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት የኮፕ32 አስተናጋጅ ሀገር ሆና መመረጧ ይታወሳል፡፡
በዚህ መሰረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በትናንትናው ዕለት የኮፕ32 ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
የኮፕ32 ተወካይ ፕሬዚዳንት መሰየምን ተከትሎ በዛሬው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ቁልፍ የዝግጅት ተግባራትን ለማቀናጀት የሚያስችል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ስብሰባ ተደርጓል።
ስብሰባው ኢትዮጵያ የኮፕ32 ጉባኤን ስታስተናግድ አካታችና በሚገባ የተሰናዳ ጉባኤ እንድታሳካ ለማረጋገጥ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየበት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡