ኢትዮጵያና ቻይና በጸጥታ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ከቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ደህንነት ትብብር ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ዋንግ ሊሲን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሽብርና በሌሎች ቀጣናዊ እንዲሁም አህጉራዊ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡
ከሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የቻይና እና የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ወደ ሁሉን አቀፍ ስትራቴጂካዊ የትብብር አጋርነት ደረጃ አድጓል።
በኢትዮጵያ የሚካሄዱትን ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ (ኮፕ 32) እና የዓለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት ኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ በስኬት ለማጠናቀቅ በትብብር ለመስራት መወያየታቸውንም ኮሚሽነር ጀነራሉ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።
እንዲሁም ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በሰው ኃይል ግንባታ ላይ በትብበር ለመስራት መወያየታቸውን አመልክተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትንና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተወጣች እንደምትገኝ በምክክሩ ወቅት ተነስቷል።
አምባሳደር ዋንግ ሊሲን ÷ ቻይና ለኢትዮጵያ የጸጥታና የደኅንነት ተቋማት በትምህርትና ስልጠና የሰው ኃይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በቁሳቁስ ድጋፍ እና በልምድና ተሞክሮ ልውውጥ እያደረገች ያለውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።
ቻይና ሽብርተኝነትንና ሌሎች ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል ከኢትዮጵያ የጸጥታና ደኅንነት ተቋማት ጋር በቅርበትና በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!