Fana: At a Speed of Life!

የሐረር ከተማን ለነዋሪዎችና ጎብኚዎች ይበልጥ ምቹ ለማድረግ…

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በሐረር ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይም በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የአባድር ፕላዛ የኮሪደር ልማት የሥራ እንቅስቃሴን ገምግመዋል።

አቶ ኦርዲን በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የአባድር ፕላዛና ሌሎች በከተማው እየተሰሩ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች የከተማዋን ገጽታ የሚቀይሩ ናቸው።

የሚከናወኑ ሥራዎች ሐረር ከተማ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ይበልጥ ምቹ እንድትሆን የሚያስችሉ መሆኑን ነው የገለጹት።

ከነዋሪዎች ጋር በመቀናጀት እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች ከአሁኑ ትውልድ ባለፈ ለቀጣዩ ትውልድ መሰረት የሚጥሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ከተማዋ ወደኋላ የቀረችባቸውን ዓመታት በሚከስ መልኩ እየተሰሩ የሚገኙ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.