Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም እና ካምቴል በካሜሩን የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን ተስማሙ

ኢትዮ ቴሌኮም እና ካምቴል በካሜሩን የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 26፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም እና የካሜሩን ቴሌኮሙኒኬሽን (ካምቴል) በካሜሩን የዲጂታል ሽግግርን ለማፋጠን የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት በካሜሩን ያውንዴ ከተማ የተፈራረሙት ስምምነት የሀገሪቱን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማፋጠን የሚያስችል የማስተር ሰርቪስ ኮንትራት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የካምቴል የስራ ኃላፊዎች ኢትዮ ቴሌኮም በ”ዲጂታል ኢትዮጵያ” ግንባታ ውስጥ ያሳየውን የላቀ የቴክኖሎጂ አመራር ከተመለከቱ በኋላ ተሞክሮውን ወደ ካሜሩን ለመውሰድ ባላቸው ፍላጎት ነው ስምምነቱ የተፈረመው፡፡

በዚህም መሰረት ሁለቱ ኦፕሬተሮች በካሜሩን የፋይናንስ ተደራሽነትን የሚያረጋግጥ የዲጂታል ክፍያ ስርዓት ለማስፋፋትና ብሔራዊ ክላውድ በመገንባት የመንግሥት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚሰሩ ይሆናል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ ለካሜሩን የዲጂታል ኢኮኖሚ ቁልፍ የሆኑ ተቋማትና ቢዝነሶች የሚያቀላጥፉ ዲጂታል መፍትሄዎችን፣ የተጨማሪ እሴት እና የኢንተርኮኔክት አገልግሎቶችን በጋራ ለመተግበር እንደሚያስችል ኢትዮ ቴሌኮም ለፋና ዲጂታል በላከው መረጃ ገልጿል፡፡

ስምምነቱ ኢትዮ ቴሌኮም የቀጣዩ አድማስ ዲጂታልና ከዚያም ባሻገር 2028 ስትራቴጂ መሰረት ድንበር ተሻጋሪ አገልግሎት በማቅረብና አህጉራዊ ትብብርን በማጎልበት የዲጂታል አፍሪካን ጉዞ ለማፋጠን የሚያስችል ምዕራፍ መሆኑ ተመላክቷል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.