Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስፋት እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ በክልሉ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ ነው አለ፡፡

የቢሮው ኃላፊ ባንችአምላክ ገ/ማርያም ለፋና ሚድያ ኮርፖሬሽን እንዳሉት ÷ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሕዝቡ የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው፡፡

በማዕከሉ የትኛውም ሰው በአግባቡ እና ምቹ በሆነ መልኩ አገልግሎት እንዲያገኝ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋቱን ጠቁመዋል።

በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ከተሞች ላይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ለማስፋት ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ አመልክተዋል፡፡

በዚህ መሰረትም በደብረብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ወልድያ፣ ደብረማርቆስ እና ደብረታቦ ከተሞች አገልግሎቱን ለማስጀመር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡፡

በቀጣይ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በ24 ከተሞች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው÷ በገጠርም መሰል ከአካባቢው ጋር የሚስማማ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ሃብታሙ ሞገስ በበኩላቸው ÷ ባለፉት 7 ዓመታት የተለያዩ የተቋም ሪፎርሞች ሲደረጉ መቆየታቸውን አስታውሰዋል፡፡

ሪፎርሙ አሰራርን ዲጂታላይዝ በማድረግ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን እና ሙስናን መቀነስ ላይ መሰረት ያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህንን ለማሳካት በሀገር፣ በክልል እና በከተሞች ደረጃ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የማስፋት ሥራ መከናወኑን አንስተዋል፡፡

ማዕከሉ ለሕብረተሰቡ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፈጣን፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ነው ያሉት፡፡

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን ከመከላከል አንጻር ሁነኛ መፍትሔ ነው ያሉት ደግሞ የአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የቴክኖሎጂ ዘርፍ አስተባባሪ ምህረቱ ሥዩም ናቸው።

ማዕከሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዲጂታላይዝ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ለተገቢ ቁጥጥር ዘመናዊ መንገድ ፈጥሯል ብለዋል፡፡

በዮናሰ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation

Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting

Facebook https://web.facebook.com/fanasport

Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate

Telegram t.me/fanatelevision

Website www.fanamc.com

TikTok www.tiktok.com/@fana_television

WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29

Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment

TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment

Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.