2ኛው የኢትዮጵያ ኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች ጠቅላላ ጉባዔ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ታሕሳስ 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 2ኛው የኢትዮጵያ ኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች ጠቅላላ ጉባዔ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡
ጉባዔው ትምህርት ሚኒስቴር ዩኒቨርሲቲዎች ባላቸው የትኩረት መስክ ልየታ መሠረት ከተከፋፈሉ በ4 ምድቦች ውስጥ የአጠቃላይ ኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች ዘርፍ ማሕበር የተዘጋጀ ነው።
የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ቶፊቅ ጀማል (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ማህበሩ በዩኒቨርሲቲዎቹ መካከል ትብብርን ለማላቅና ውጤታማ ሥራዎችን ለማከናወን ወሳኝ ሚና አለው።
የኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች የተሰጣቸውን ተልዕኮ ለማሳካትና ተወዳዳሪ ተቋማት ለማድረግ መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የማህበሩ ሰብሳቢ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት አነጋግረኝ ጋሻው (ዶ/ር) ከአዲሱ የማህበሩ ሰብሳቢ የጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ድሪባ ኢቲቻ (ዶ/ር) ጋር የሰነድ ርክክብ አድርገዋል።
በጉባዔው ላይ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይን ጨምሮ የማህበሩ አባል ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።
በአንዷለም ተስፋዬ