የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ለብሔራዊ ጥቅም መከበር ሚናውን እንዲወጣ ይሰራል – ኦርዲን በድሪ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ለብሔራዊ ጥቅም መከበር እና ለሀገራዊ አንድነት መረጋገጥ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ይሰራል አሉ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ዘርፉን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራሮች ጋር በተወያዩበት ወቅት እንዳሉት፤ በክልሉ አሰባሳቢ ትርክቶች የበላይነትን እንዲይዙ እየተሰራ ነው።
የአንድነትና የወንድማማችነትን እሴት በማጎልበት ማህበረሰቡ ለልማት ስራዎች ተባባሪ እንዲሆን በማስቻል ረገድ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የጎላ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸው፤ ለዘርፉ ውጤታማነት በግብአትም ሆነ በሰው ኃይል ልማት ድጋፍ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
ከለውጡ ወዲህ የማህበረሰቡን ዘርፈ ብዙ የመልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት በቁርጠኘነት እየተሰራ መሆኑንና እስካሁንም አበረታች ውጤት መገኘቱንም አንስተዋል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ በበኩላቸው፤ በክልሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የሚደነቁ ናቸው ብለዋል።
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ብሔራዊ ጥቅምን በተመለከተ ግንዛቤ በበመፍጠር ሀገራዊ አንድነትን ለማጎልበት ትልቅ ሀላፊነት እንዳለበት ጠቁመዋል።
በመሆኑም በዘርፉ ያሉ ማነቆዎችን ከክልሎች ጋር በቅንጅት በመስራት እንዲፈቱ ለማስቻል እንደሚሰራ መናገራቸውን የሐረሪ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሄኖክ ሙሉነህ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook WMCC
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!