በአፍሪካ ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ አንጎላን አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ሁለት የመጀመሪያ ጨዋታ ደቡብ አፍሪካ አንጎላን 2 ለ 1 በማሸነፍ መርሐ ግብሩን በድል ጀምራለች፡፡
የደቡብ አፍሪካን የማሸነፊያ ግቦች ኦስዊን አፖሊስ እና ለይል ፎስተር ከመረብ ሲያሳርፉ፥ የአንጎላን ብቸኛ ግብ ደግሞ ሾው አስቆጥሯል።
ቀደም ሲል አመሻሽ 11:00 ሰዓት ላይ በተደረ ሌላኛው የምድብ ጨዋታ ማሊ እና ዛምቢያ 1 አቻ ተለያይተዋል።
በጨዋታው ላሲን ሲናዮኮ የማሊን ግብ ሲያስቆጥር ፓትሰን ዳካ የዛምቢያን ግብ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
ዛሬ የሚካሄዱ የምድብ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲያሆሄዱ ምሽት 5:00 ሰዓት ላይ ግብፅ ከዚምባብዌ ጋር ይገናኛሉ።