Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ፍላጎት ማስጠበቂያ ተደርገው ቆይተዋል – ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ትምህርትና ፖለቲካ በመደበላለቃቸው የትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ፍላጎት ማስጠበቂያ ተደርገው ቆይተዋል አሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር)፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር ተወያይተዋል።

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በወቅቱ እንዳሉት፤ ባለፉት ዓመታት የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋት ቢሰራም ከትምህርት ጥራት አንፃር የትምህርት ሥርዓቱ ችግር ውስጥ ገብቶ ቆይቷል፡፡

ትምህርትና ፖለቲካ በመደበላለቃቸው የትምህርት ተቋማት የፖለቲካ ፍላጎት ማስጠበቂያ ተደርገው መቆየታቸውንም አንስተዋል።

በትምህርት ዘርፍ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በዘርፉ በርካታ የሪፎርም ተግባራት ተቀርፀው እየተተገበሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ኢትዮጵያ ባላት ፀጋዎች ዙሪያ ትርጉም ያላቸው ፈጠራ፣ ጥናትና ምርምር የሚደረግባቸው ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን የዩኒቨርሲቲ አመራር ምደባ ከመንደር ወጥቶ በውድድር እንዲሆን እየተደረገ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ባይሳ ለታ (ዶ/ር) በበኩላቸው ውጤታማ ለመሆን ለጥራት ትኩረት መስጠት ይጠበቅብናል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.