Fana: At a Speed of Life!

ከቡና ወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀምና የምርት ጥራትን በማስጠበቅ ከቡና ወጪ ንግድ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ እየተሰራ ነው አሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)።

በክልሉ ሸካ ዞን የዘመናዊ ቡና ልማት ኢኒሼቲቭ ማስጀመሪያና ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እየተካሄደ ነው።

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ የቡና ልማት ለክልሉም ሆነ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት የጀርባ አጥንት መሆኑን አውስተዋል፡፡

ንቅናቄው አርሶ አደሩን ካለበት የባህላዊ አሰራር ወደ ዘመናዊና ውጤታማ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት የሚያሸጋግር ቁልፍ ኢኒሼቲቭ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢኒሼቲቩ ዓላማ ምርትን መጨመር ብቻ ሳይሆን የቡና ጥራትን በማስጠበቅ በዓለም ገበያ ተወዳዳሪና ተመራጭ መሆን ነው፤ ይህም የውጭ ምንዛሪን ለማሳደግ ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡

የቡና ልማቱ እንደ አንድ ትልቅ የኢኮኖሚ ንቅናቄ ተወስዶ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በከፍተኛ ትጋት ከተመራ የዜጎችን ሕይወት በአጭር ጊዜ መለወጥ እንደሚቻል አጽንኦት መስጠታቸውንም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ የሺዋስ ዓለሙ ለፋና ዲጂታል ገልጸዋል።

በዘመናዊ ቡና ልማት ኢኒሼቲቭ በመጀመሪያ ዙር 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በ400 ሄክታር መሬት ላይ በጠብታ መስኖ እርሻ እንደሚጀመርም ተናግረዋል።

በመድረኩ ላይ የክልልና የዞን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎች፣ አርሶ አደሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በአድማሱ አራጋው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation
Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting
Facebook https://web.facebook.com/fanasport
Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate
Telegram t.me/fanatelevision
Website www.fanamc.com
TikTok www.tiktok.com/@fana_television
WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.