Fana: At a Speed of Life!

የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ ነው – አቶ አረጋ ከበደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ባለፉት ዓመታት በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ስራዎች ተጨባጭ ለውጥ እያመጡ ነው አሉ፡፡

ርዕሰ መስተዳደሩ የዘንድሮውን ክልላዊ የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት በአርጎባ ብሔረሰብ ልዩ ወረዳ ተገኝተው በደለመኔ ተፋሰስ በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት÷ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ስራው እርጥበትን በመጨመር ለተፈጥሮ ሚዛናዊነት ሚናውን እየተወጣ ነው፡፡

ተፈጥሮን መንከባከብ በተፈጥሮ እና በሰው ልጅ መካከል ያለውን ግንኙነት ከማደስ ባለፈ በግብርና ዘርፍ ምርታማነትን በመጨመር የሚታይ ለውጥ እንዲመጣ ማድረጉን ተናግረዋል።

በክልሉ በዛሬው እለት በተጀመረው የተቀናጀ ተፋሰስ ልማት ከ450 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት እንደሚለማ ገልጸው÷ ዕቅዱን ለማሳካት ማህበረሰቡ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል።

የተቀናጀ ተፋሰስ ልማቱን በስነ ህይወታዊ ዘዴ የማስተሳሰር ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በከድር መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.