Fana: At a Speed of Life!

ውይይት እና ንግግር ለሀገራዊ አንድነት…

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በምክክር እና ውይይት ችግሮችን መፍታት ለዜጎች አንድነትና ለሀገር ብልጽግና ትልቅ ሚና ይጫወታል አሉ የሕግና ማሕበረሰብ ሳይንስ ምሁራን።

ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ቆይታ ያደረጉት የሕግና የፖለቲካ ሳይንስ ተመራማሪ ዓለማየሁ ገብረማሪያም (ፕ/ር) እና ጋዜጠኛና የማሕበረሰብ ጥናት ተመራማሪ መሐመድ ሲራጅ ውይይትና እና ንግግር ሀገርን ወደ ብልጽግና ለማሻገር የማይተካ ሚና አላቸው ብለዋል።

ዓለማየሁ ገብረማሪያም (ፕ/ር) ከ40 በላይ ሀገራት በምክክር ችግሮቻቸውን መፍታት መቻላቸውን ገልጸው÷ ለብልጽግናቸው ሲሉ ቅራኔያቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ በመፍታት አሁን ላይ ተገዳዳሪና በኢኮኖሚ የበለጸገ ሀገር መገንባታቸውን አስረድተዋል።

ቱኒዝያ፣ ኬንያ እና ደቡብ አፍሪካ ከአፍሪካ የሚጠቀሱ ሀገራት ናቸው ያሉት ተመራማሪው÷ ከደቡብ አሜሪካም አርጀንቲናን ጨምሮ በርካታ ሀገራት ስኬታማ የምክክር ሂደት ማካሄዳቸውን ጠቅሰዋል።

ጋዜጠኛ መሐመድ ሲራጅ በበኩላቸው÷ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ ችግሮቻቸውን በውይይትና ንግግር ከፈቱ ሀገራት ተሞክሮ መውሰድ እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡

ስብራቶቻችንን ለመጠገን በምናደርገው ጥረትም ንግግር እና ውይይት ምን ያህል ዋጋ እንዳላቸው የሚያመለክቱን ናቸው ብለዋል።

በኢትዮጵያ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ለዘመናት ሲንከባለሉ የቆዩ የሐሳብ ልዩነቶችና አለመግባባቶች በምክክር ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል።

በወንድሙ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.