Fana: At a Speed of Life!

የገና በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ዓለም ሀገራት ተከብሯል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተለያዩ ሁነቶች በትናንትናው ዕለት በድምቀት ተከብሯል፡፡
የገና በዓል የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን በማሰብ የሚከበር ሲሆን÷ በዓሉ በታሕሣሥ ወር በ29ኛው ቀን ይከበራል።
በአራት ዓመት አንድ ጊዜ ደግሞ በዘመነ ዮሐንስ ታሕሣሥ 28 ይከበራል፡፡
የጎርጎሮሳውያኑን የዘመን ቀመር የሚከተሉ ሀገራት በታሕሣሥ 16 (ዲሴምበር 25) የገና በዓልን የሚያከብሩ ሲሆን፤ የጁሊያን የዘመን ቀመር የሚከተሉ ሀገራት ደግሞ በታሕሳስ 29 (ጃንዋሪ 7) የገና በዓልን ያከብራሉ።
በትናንትናው ዕለት ከኢትዮጵያ ጋር የገና በዓልን ሩሲያ፣ ግብጽ፣ ሰርቢያ እና ኤርትራ በዓሉን ያከበሩ ሀገራት ናቸው።
ዩክሬን ቀደም ሲል በዓሉን በታሕሣሥ 29 ታከብር የነበረ ሲሆን፤ ከፈረንጆቹ 2023 ወዲህ ግን በመንግሥት ውሳኔ በዓሉ ታሕሣሥ 16 ቀን እየተከበረ ይገኛል።
ይሁን እንጂ በርከት ያሉ ዩክሬናውያን የክርስትና እምነት ተከታዮች በትናንትናው ዕለት በዓሉን አክብረው ውለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.