የ’ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ’ የሩጫ ውድድር በደብረብርሃን ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥር 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ቱሪዝም ሚኒስቴር ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የ’ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክ 2018’ የሩጫ ውድድር በደብረብርሃን ከተማ ተካሂዷል።
ውድድሩ ከዚህ በፊት በአራት የተለያዩ ከተሞች ይደረግ የነበረ ሲሆን በዚህ ዓመት ደብረብርሃን እና ሀረርን በማካተት በስድስት ከተሞች ይደረጋል።
በስፖርት ቱሪዝምን ማስተዋወቅ የውድድሩ አንድ አካል ሲሆን ተሳታፊዎች በአንኮበር ቤተ መንግሥት ጉብኝት አድርገዋል።
በውድድሩ በወንዶች አትሌት ስጦታው ሰማኸኝ፣ ቦጋለ ሰለሞን እና አየለ ከበደ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ አጠናቅቀዋል።
በሴቶች ደግሞ አትሌት አማረች ገብሬ፣ ደመቅ ጥላሁን እና የዘብነሽ ወንዴ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ውድድሩን ጨርሰዋል።
በውድድሩ ከ1ኛ እስከ 5ኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በእንዳልካቸው ወዳጄ