ሀዲያ ሆሳዕና ምድረ ገነት ሽረን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 15ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዲያ ሆሳዕና ምድረ ገነት ሽረን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕናን ግቦች ብሩክ በየነ በፍጹም ቅጣት ምት፣ ኤልያስ አህመድ እና ሱራፌል ተመስገን ሲያስቆጥሩ፤ ተካልኝ ደጀኔ የምድረ ገነት ሽረን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል።
ቀደም ሲል በተካሄዱ ጨዋታዎች ነገሌ አርሲ ከወላይታ ድቻ 1 ለ 1፤ ሸገር ከተማ እና ፋሲል ከነማ ደግሞ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።