Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ በተኪ ምርቶች ከ20 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪን ማስቀረት ተችሏል

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በግማሽ በጀት ዓመት በተኪ ምርቶች ከ20 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪን ማስቀረት ተችሏል አለ የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢኖቬሽን ቢሮ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዘመድኩን ሰሎሞን እንዳሉት÷ በክልሉ ለኢንዱስትሪ ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሪ ወጪን ለመቀነስ እየተሰራ ነው።

በእንጨትና ብረታ ብረት እንዲሁም በጨርቃጨርቅና ኬሚካል ውጤቶች ላይ በክልሉ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ከ20 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ወጪን ማስቀረት ትችሏል ነው ያሉት።

በክልሉ ኢንዱስትሪዎች በግብርና ዘርፍ በመሰማራት የቅመማቅመም እንዲሁም የማር ምርትን አቀነባብሮ ለውጭ ገበያ በማቅረብ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት መቻሉንም ጠቁመዋል።

በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለውን አቅም አሟጥጦ መጠቀም ይገባል ያሉት ኃላፊው÷ ኢንዱስትሪዎቹ የሚፈልጉትን የብድር እና መሠረተ ልማት አቅርቦቶችን ለማሟላት እንደሚሰራም አመልክተዋል።

በፍሬው አለማየሁ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.