Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ዩናይትድ ለኮቢ ማይኑ አዲስ ውል ለማቅረብ ዝግጁ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ወጣቱን አማካይ ኮቢ ማይኑ ለረዥም ዓመታት በክለቡ ለማቆየት አዲስ ውል የማቅረብ ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል፡፡

የ20 ዓመቱ እንግሊዛዊ በፈረንጆቹ 2023 ከማንቼስተር ዩናይትድ አካዳሚ ወደ ዋናው ቡድን ካደገ ወዲህ ለክለቡ ባደረጋቸው 87 ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡

ተጫዋቹ በተለይም በዘንድሮው የውድድር ዓመት በአሰልጣኝ ሩበን አሞሪም በቂ የመሰለፍ እድል አለማግኘቱን ተከትሎ በዚህ የጥር የዝውውር መስኮት ከክለቡ እንደሚለቅ በስፋት ሲዘገብ ቆይቷል፡፡

የአሰልጣኝ ሩበን አሞሪምን ስንብት ተከትሎ በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ወደ ኃላፊነት የመጣው ማይክል ካሪክ ተጫዋቹን በቋሚነት የመጠቀም ፍላጎት እንዳለው እየተነገረ ይገኛል፡፡

ባሰለፍነው ቅዳሜ በውድድር ዓመቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊጉ በቋሚነት በጀመረበት የማንቼስተር ደርቢ ጨዋታ ላይ ጥሩ እንቅስቃሴ ማሳየቱ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎ ክለቡ ለወጣቱ አማካይ አዲስ ውል ለማቅረብ ፍላጎት እንዳለውና ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር የመጀመሪያ ደረጃ ንግግር ማድረጉን ስካይ ስፖርት ዘግቧል፡፡

ብራዚላዊው አማካይ ካሴሚሮ በመጪው ክረምት ከኦልድትራፎርድ እንደሚለቅ ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ዩናይትድ ለኮቢ ማይኑ አዲስ የረዥም ጊዜ ውል ለማቅረብ ዝግጁ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.