ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽረ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ17ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ምድረ ገነት ሽረ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ወጥተዋል፡፡
በጨዋታው የምድረ ገነት ሽረ ተጫዋች ስንታየሁ ወለጬ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ተሰናብቷል፡፡
የሊጉ ጨዋታ ሲቀጥል በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከመቻል ይገናኛሉ፡፡
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ደግሞ ቀን 10 ሰዓት ላይ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከወላይታ ድቻ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡