Fana: At a Speed of Life!

አይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት በይፋ ተመርቋል፡፡

ኢትዮጵያ አይሻ-2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን በይፋ በመመረቅ በኢነርጂ ዘርፉ ላይ አዲስ ታሪክ የጻፈ ታላቅ እጥፋት አስመዝግባለች ሲል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል፡፡

ይህ ውጤት የታዳሽ ኃይል አማራጮችን ለማስፋፋት መንግሥት የወሰደው ወሳኝ ርምጃ ምልክት መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

የተረጋጋ የኃይል አቅርቦት በቴክኖሎጂ ለሚመራ ኢኮኖሚ ዋነኛው የጀርባ አጥንት መሆኑን አመልክቷል፡፡

ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ያላትን ርዕይ ወደ ተግባር ለመለወጥ ቁርጠኛ ብቻ ሳትሆን ከፍ ያሉ ርዕዮቿን ለመፈፀም በቂ አቅም ያላት መሆኑን በተግባር አሳይቷልም ነው ያለው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.