Fana: At a Speed of Life!

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 10ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-

👉 መፈናቀልን በሚመለከት ኢትዮጵያውያን በፈለጉት አካባቢ ሰርተው መኖር ሕገመንግሥታዊ መብታቸው ነው።

👉 የተፈናቀሉ ሰዎች መመለስ ይፈልጋሉ፣ ቀድሞ የነበሩበት አካባቢ ይምጡልን ይላል፤ ማን ነው የያዛቸው?

👉 በወልቃይት አካባቢ ተፈናቃዮችን የመመለስ ስራ ሊፈታ ያልቻለ አስቸጋሪ ጉዳይ ነው።

👉 ገበሬ ዘር ዘርቶ እህል እንደሚጠብቀው ሁሉ የተፈናቀለውን አትሄድም ብለው ይዘው ስደት፣ መፈናቀል፣ ስቃይ በመዝራት ከሌሎች ኃይሎች ርዳታ የሚጠብቁ አሉ።

👉 ተፈናቃይ ያልተመለሰበት አካባቢ ሰው መመለስ ስላልፈለገ ሳይሆን ተፈናቃይን መያዣ ያደረገ ፖለቲካ ኢትዮጵያ ውስጥ በመኖሩ ነው።

👉 አንዳንድ ፓርቲዎች ተፈናቃይን የራስ ሕልውና ማቆያ ያደርጓቸዋል፤ ይህንን ለማሻሻል ብዙ ሙከራ እና ስራዎች ተሰርተዋል።

👉 የወልቃይት አካባቢ ነዋሪዎች ከየትኛውም የኢትዮጵያ አካባቢ ቢፈናቀሉ ወልቃይት ውስጥ በሰላማዊ መንገድ መኖር መብታቸው ነው፤ የፌዴራል መንግሥትም በጽኑ የሚያምነው ጉዳይ ነው።

👉 በወልቃይት ጉዳይ በአማራ እና በትግራይ ክልል መካከል የይገባኛል ጥያቄ ለረጅም ጊዜ የቆየ ነው፤ የፌዴራል መንግሥት ሐሳብ ሰው ሳይፈናቀል ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ራሱ በሕዝበ ውሳኔ ይወስን የሚል ነው።

👉 የወልቃይትን ጉዳይ የሚወስነው የዚያው አካባቢ ሰው ነው፤ ለዚህም ፓርቲዎች አስቻይ ሁኔታን መፍጠር አለባቸው።

በዮናስ ጌትነት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.