Fana: At a Speed of Life!

ማንቼስተር ሲቲ ከኒውካስል …

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በካራባኦ ካፕ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድ የመልስ ጨዋታቸውን ያካሂዳሉ።

በግማሽ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ወደ ሴንት ጀምስ ፓርክ አቅንቶ 2 ለ 0 ማሸነፍ የቻለው ማንቼስተር ሲቲ በዌምብሌይ ለሚደረገው የፍጻሜ ጨዋታ ለማለፍ ዛሬ ምሽት 5 ሰዓት ላይ ኒውካስልን ያስተናግዳል።

የአምናው ሻምፒየን ኒውካስል ወደ ፍጻሜው ለማለፍ በኢትሀድ ስታዲየም ጠንካራ ፍልሚያ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

በመጀመሪያ ዙር የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ድል አድርጎ የተመለሰው የፔፕ ጓርዲዎላው ሲቲ ወደፍጻሜ የማለፍ ቅድመ ግምት ተሰጥቶታል።

የማንቼስተር ሲቲ እና የኒውካስል ዩናይትድ አሸናፊ ትናንት ምሽት ቼልሲን በማሸነፍ ለፍጻሜ ከደረሰው አርሰናል ጋር ለዋንጫ ይፋለማል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.