ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ ውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ኦሊቪየር ዣን ፓትሪክ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ የጋራ ፍላጎቶች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ኦሊቪየር ዣን ፓትሪክ በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ በአፍሪካ ወሳኝ የሩዋንዳ አጋር ሀገር መሆኗን አውስተዋል፡፡
የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ከ48ኛው የአፍሪካ ሕብረት መደበኛው የሥራ አስፈጻሚዎች ስብሰባ ጎን ለጎን በተካሄደው ውይይት ሁለቱ ወገኖች በቀጣናዊና አሕጉራዊ ሰላም እና ጸጥታ ዙሪያ ሀሳብ ተለዋውጠዋል፡፡