Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን ለ8 ወራት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንን የስራ ዘመን ለ8 ወራት እንዲራዘም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አጸደቀ።
ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው የ5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የኮሚሽኑን የእስካሁን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ተወያይቶ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፤ ባለፉት አራት ዓመታት በሀገር ውስጥና በውጭ የተካሄዱ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተሳታፊ ልየታ ተግባራትን በዝርዝር አቅርበዋል።
በምክር ቤቱ የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቱ አለነ፥ ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት ለቀጣይ የምክክር ሂደቱ ተግባራት ወሳኝ መሰረት የሚጥሉ ሥራዎችን አከናውኗል ብለዋል።
በቀጣይም ቀሪ ሥራዎችን እንዲያጠናቅቅ ተጨማሪ የስምንት ወራት ጊዜ እንዲሰጠው ለምክር ቤቱ ያቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን የምክር ቤቱ መረጃ አመልክቷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.