Fana: At a Speed of Life!

የደረቅ ወደብ ጭነቶች የበይነ መረብ ምዝገባ ማሻሻያ…

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ደረቅ ወደቦች ላይ በበይነ መረብ የሚሰጠው የጭነት አገልግሎት መመዝገቢያ ስርዓት ማሻሻያ ተደርጎበታል።
የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማሕበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) እንዳሉት÷ የተደረገው ማሻሻያ የደረቅ ወደብ አገልግሎት አሰጣጥን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ለመቀየር የሚደረግ ጥረት አካል ነው።
በዚህም ወደ ውጭ የሚላኩ እና ወደ ሀገር የሚገቡ ጭነቶች አጠቃላይ ሂደትን በዲጂታል ስርዓት ማካተት መቻሉን ገልጸው÷ ስርዓቱ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ የመስመር ላይ ክፍያ እና የማረጋገጫ አገልግሎቶችን የሚያካትት መሆኑን አስረድተዋል።
አዲሱ አሃዛዊ አሰራር የእቃ መከታተያ ያለው በመሆኑ ደንበኞች ጭነቶቻቸውን በቀላሉ እንዲቆጣጠሩ ያስችላልም ነው ያሉት።
የጭነቶች ምዝገባ በዲጂታል ስርዓት መከወኑ በጭነት አያያዝ ላይ ያለውን ውጤታማነት እንደሚጨምር አመልክተዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.