1 ሚሊየን ብር ሽልማት የሚያስገኘው የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሙዚቃ ውድድር…
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በትብብር ባዘጋጁት የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሙዚቃ ውድድር ተወዳዳሪዎች ስራዎቻቸውን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡
ተቋማቱ በትብብር ባዘጋጁት የሰው ሰራሽ አስተውሎት የሙዚቃ ውድድር አሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የ1 ሚሊየን ብር ሽልማት ይበረከታል፡፡
ውድድሩ የኢትዮጵያን የፈጠራ ኢንዱስትሪ ወደ አዲስ የቴክኖሎጂ ምዕራፍ ለማሸጋገር እንዲሁም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በመታገዝ የኢትዮጵያን የጀግንነት ታሪክ በተለይም የዓድዋ ድልን ለመዘከር ያለመ ነው፡፡
በውድድሩ ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው በርካታ ተወዳዳሪዎች ስራዎቻቸውን ያስረከቡ ሲሆን፥ የሙዚቃ ስራዎች የማስረከቢያ ጊዜ እስከ መጋቢት 14/2018 ዓ.ም ድረስ ተራዝሟል፡፡
ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የቀረበውን ሊንክ በመጠቀም ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘትና ስራዎቻቸውን ማስረከብ ይችላሉ፡፡ 👇
https://www.creativeaward.ai/