Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጣሊያን የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት በመፈራረም ያላቸውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት አጠናክረዋል።

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ እና የጣሊያን የኢኮኖሚና ፋይናንስ ሚኒስትር ጂያንካርሎ ጆርጌቲ ተፈራርመዋል።

የዕዳ ሽግሽግ ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ስትራቴጂካዊ የልማት አጋርነት ይበልጥ የሚያጠናክርና የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የሚደግፍ መሆኑ ተመላክቷል።

የተፈረመው የሁለትዮሽ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት በቡድን 20 ሀገራት የጋራ ማዕቀፍ ሥር ይፋዊ አበዳሪዎች ኮሚቴ በሚመራው ሒደት መሰረት የተከናወነ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

አቶ አሕመድ ሺዴ በዚህ ወቅት ÷ የዕዳ ሽግሽግ ስምምነት ላይ ለመድረስ እና የሁለትዮሽ ስምምነቱን በተሳካ ሁኔታ ለመጨረስ ጣሊያን ለተጫወተችው ገንቢ ተሳትፎና አመራር አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

ጂያንካርሎ ጆርጌቲ በበኩላቸው÷ ስምምነቱ ከኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቁልፍ አጋር የሆነችበትን የጣሊያን ማቲ ፕላን ለአፍሪካ አስተዋፅኦ እንዳለው መማልከታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.