Fana: At a Speed of Life!

ለምርጫ የተመዘገቡ ዜጎች ቁጥር 18 ሚሊየን 556 ሺህ 337 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እስከ ትናንት ባካሄደው የመራጮች ምዝገባ 18 ሚሊየን 556 ሺህ 337 ተመዝግበዋል፡፡

ቦርዱ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫን የመራጮች ምዝገባ በጊዜ ሠሌዳው መሠረት ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በማከናወን ላይ ይገኛል።

በዚህም እስከ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም በማንዋልና በዲጂታል አማራጭ ባከናወነው የመራጮች ምዝገባ 18 ሚሊየን 556 ሺህ 337 መራጮች መመዝገባቸውን አስታውቋል።

ከተመዘገቡት መራጮች ውስጥ 10 ሚሊየን 133 ሺህ 639 ወንድ ሲሆኑ፤ 8 ሚሊየን 422 ሺህ 698 ሴት መሆናቸውን ቦርዱ ባወጣው መረጃ አመላክቷል።

ቦርዱ ለመራጮች ምዝገባ አወዳድሮና ገለልተኝነታቸውን በፖለቲካ ፓርቲዎች አስተችቶ ያሰለጠናቸውን 187 ሺህ 28 የምርጫ አስፈጻሚዎች ማሰማራቱንም አስታውሷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.