Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የተለያዩ ተቋማት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ አድርገዋል፡፡

የኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የ3 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት፤ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው ድንገተኛ አደጋ የሁሉንም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ልብ የሰበረ ነው ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱ በአደጋው ሳቢያ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ጥረት ማድረጉን ገልጸው፤ በዜጎች ላይ ተመሳሳይ ችግር እንዳይከሰት በሁሉም አካባቢ አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ እንዲደረግም አሳስበዋል፡፡

በተመሳሳይ የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በጋሞ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች 3 ሚሊየን ብር እና 100 ኩንታል ዱቄት የዓይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም የተባበሩት መንግስታት የሥነ ሕዝብ ፈንድ (ዩኤንኤፍፒኤ) 2 ሚሊየን 621 ሺህ 618 ብር ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አድርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.