Fana: At a Speed of Life!

የዜጎችን የታዳሽ ሃይል ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዜጎችን የታዳሽ ሃይል ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው አለ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፡፡
ሚኒስቴሩ በካፋ ዞን አዲዮ ወረዳ ያስገነባውን የሶላር ሚኒግሪድ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ፕሮጀክቱ ከሶላር ሚኒግሪድ 300 ኪሎ ዋት ሃይል በማመንጨት 1 ሺህ 500 አባወራዎችን የኤሌክትሪክ ሃይል ተጠቃሚ ማድረግ ያስችላል፡፡
የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴዔታ ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የማሕበረሰቡን የታዳሽ ሃይል ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ መሰል ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡
ባለፉት ሁለት ወራት 10 ፕሮጀክቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን ጠቁመው÷ በቀጣይ አንድ ወር ውስጥ 6 ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ ም/ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ማስረሻ በላቸው በበኩላቸው÷ፕሮጀክቱ የነዋሪዎችን ጥያቄ በተግባር በመፍታት ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን ያረጋገጠ መሆኑን አንስተዋል።
በአሸናፊ ሽብሩ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.