Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት አፍሪካ ከፖሊዮ ነፃ መሆኗን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 20፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት አፍሪካ ከፖሊዮ ነጻ መሆኗን አስታውቋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት አፍሪካ ከተፈጥሯዊ ፖሊዮ ነፃ መሆኗን ነው የገለጸው፡፡

የአህጉሪቱ ከፖሊዮ ነጻ መባል ለ30 ዓመታት ፖሊዮን ለማጥፋት የተካሄደው ዘመቻ ወሳኝ እርምጃ ነውም ተብሏል፡፡

በአሁኑ ወቅት ፖሊዮ ዓለም ላይ በአፍጋኒስታን እና ፓኪስታን ብቻ እንደሚገኝም ነው የተነገረው፡፡

ሆኖም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለፖሊዮ ክትባት ለማግኘት የሚደረጉ ጥረቶችን እያስተጓጎለ ነው ተብሏል ፡፡

በአህጉሪቱ ለመጨረሻ ጊዜ የፖሊዮ ተጠቂ የተገኘው ከአራት አመታት በፊት በናይጀሪያ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-አልጀዚራ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.