ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ሠራተኞች ጋር ማዕድ በመቋደስ በዓል አከበሩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በመዲናዋ ትላልቅ ፕሮጀክቶች ሠራተኞች ሠራተኞች ጋር ማዕድ በመቋደስ የትንሣኤ በዓልን አክብረዋል።
ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ በአዲስ አበባ እውን እየሆኑ ባሉ ትላልቅ ፕሮጀክቶች የሚሰሩ ባለሙያዎች 24/7 ያለእረፍት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
የበዓልን ቀን ጭምር በስራ ላይ ካሉ የአቃቂ ኢንዱስትሪ ክላስተር ባለሙያዎች እና ሠራተኞች ጋር በመሆን ማዕድ በመቋደስ የትንሳዔ በዓልን አብረን አክብረናል ብለዋል።
መስራት ያስከብራል፣ ድህነት ያዋርዳል ያሉት ከንቲባዋ÷ በዓላችን ሙሉ የሚሆነው ሰርተን ስንበለፅግ ነው ብላችሁ ቀን ከሌሊት ሳትሉ ዛሬም ስራ ላይ የምታሳልፉ ሁሉ እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል፡፡
በዓሉን በጋራ ሆነን ማዕድ ስንቋደስ ለህዝባችሁ እንዲሁም ለከተማችሁ እድገት የምታደርጉትን አስተዋፅኦ እንዲሁም ለድካማችሁ እውቅና እንዲሆንና በርቱ ለማለት ነው ሲሉም ገልጸዋል።