Fana: At a Speed of Life!

በነጻ የንግድ ቀጣናዎች የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነጻ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብዓቶችንና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ ተፈቅዷል አለ የገንዘብ ሚኒስቴር።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ÷ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ልማትን ወደኋላ የሚይዙ የካፒታል እጥረት፣ የግብዓት አቅርቦት ችግር እና የባለሙያ እጥረት ደረጃ በደረጃ በማቃለል ረገድ በርካታ ስራዎችን እየሰተራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከነዚህም መካከል አስመጪዎች ግብዓቶችንና ምርቶችን ቀረጥና ታክስ ሳይከፍሉ ወደ ሀገር ውስጥ አስገብተው ለግብዓቱ ወይም ለምርቱ ገበያ ባገኙ ጊዜ ቀረጥ እና ታክሱን የሚከፍሉበትን አሰራር የሚፈቅድ የነጻ የንግድ ቀጣና አሰራር መዘርጋቱ ይታወሳል።

አሁን ደግሞ የንግድ ቀጣናዎች ባለሃብቶችን የበለጠ የሚስቡ እንዲሆኑ ለማድረግ በነጻ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ ተሰማርተው ግብዓቶችን እና ምርቶችን ለገበያ በማቅረብ ስራ ላይ የተሰማሩ ባለሃብቶች ከገቢ ግብር ነጻ እንዲሆኑ መፈቀዱን አመልክቷል።

ባለሃብቶቹ እድሉን በመጠቀም በነጻ የንግድ ቀጣናዎች ውስጥ እንዲሰማሩ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.