Fana: At a Speed of Life!

የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይ በዓድዋ ድል መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት÷ ዛሬ የላይቤሪያ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ንዩማ ቦአካይን በዓድዋ ድል መታሰቢያ በክብር ተቀብለናል ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ በዓድዋ ጀግኖች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠው፣ ለመላው ጥቁር ህዝቦች ነጻነት ፋና ወጊ የሆነውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም መጎብኘታቸውን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያና ላይቤሪያ ከአፍሪካ ሀገራት በቅኝ ግዛት ስር ያልወደቁ የጥቁር ህዝቦች ኩራት እና የፀረ ቅኝ ግዛት ንቅናቄ መሰረቶች መሆናቸው እንደሚታወቅ የገለጹት ከንቲባዋ፤ ፕሬዚዳንቱ በምድረ ቀደምቷ ኢትዮጵያና በአፍሪካውያን ርዕሰ መዲና አዲስ አበባ የሚኖራቸው ጉብኝት የተሳካ እንዲሆን ተመኝተዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.